መስከረም ወር እንደ ሀገር በበርካታ የአደባባይ በዓላት ይደምቃል። በህብረ - ብሔራዊቷ አዲስ አበባም በህብር የሚያደምቁን ፣ በርካታ የሀገር ወስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኝዎችም የሚሳተፉባቸው የከተማችን ድምቀት የሆኑ የአደባባይ በዓላት ይከበራሉ።
በነገው ዕለት የሚከበረው የመስቀል ደመራ እና በቀጣይ የሚከበረው የእሬቻ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ ከላይ እስከ ታች ያለው አመራር ህዝባችን በማስተባበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል።
በዛሬው ዕለትም በየደረጃው ከሚገኘው አመራር እና ባለድርሻ አካላት ጋር የበዓላት አከባበር እጅግ ባማረና በደመቀ መልኩ ለማክበር የሚያስችል ቅድመ ዝግጆቶች መጠናቀቁን በግምገማዎቻችን አረጋግጠናል። በቀሪ ጊዜያትም የሚቀሩ ጉዳዮች ካሉ የምናጠናቅቅ ይሆናል።
በዓላቱ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩና ወንድማማችነትን እንዲሁም እህትማማችነትን ይበልጥ እንዲያጠናክሩ ሁላችንም ሚናችንን ማጠናከር ይገባናል።
አቶ ሞገስ ባልቻ :- በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ ፅ/ ቤት ሀላፊ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.