እንደ ስሟ ውብ አበባ እየሆነች የምትገኘው ከተማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

እንደ ስሟ ውብ አበባ እየሆነች የምትገኘው ከተማችን የብልፅግና ተምሳሌትነቷን ታጠናክራለች !

ታሪኳን ፣ አህጉራዊ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ ሀላፊነቷን የሚመጥን የከተማነት ስታንዳርድ ሳታሟላ ለዘመናት የቆየችው አዲስ አበባ አሁን ላይ ስሟን ወደ ሚመጥን ከፍታ እየወጣች ትገኛለች። 

ቀን ከሌት እየተደረገ በሚገኘው ርብርብ ጎስቋላ የነበሩ ሰፈሮቿ እየተዋቡ ሲሆን የመሰረተ ልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችም እየተፈቱ ነው፡፡ 

የህዝባችንን ተደራራቢ ችግሮች እየቀረፈ የሚገኘው ልማታችን ውጤቱ ብቻም ሳይሆን ሂደቱም የህዝባችንን ተሳታፊነት እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ልማታችን ወደ ነበርነት እየተቀየሩ የሚገኙና በደረሰባቸው ከፍተኛ ብክለት ለነዋሪዎችም የኑሮ ስጋት የሆኑ ወንዞችንም ለማፅዳት እና ህልውናቸውን በመታደግ የከተማችን ተጨማሪ መስህብ ለማድረግ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች በተጨባጭም ውጤት አስመዝግበዋል።

በቅርቡም ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ሁለተኛውን የኮሪደር ልማት ሲያስጀምሩ የቀበና ወንዝ ተፋሰስም እንደሚለማ መግለፃቸው ይታወሳል።

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን አቅጣጫ በመከተልም በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና ሌሎችም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ህዝባችንን ባሳተፈ መልኩ ልማቱን ለማከናወን አበረታች እርምጃዎች ተጀምረዋል።

በዛሬው ዕለትም በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና ሌሎች የከተማ ፣ የክ/ከተማ እንዲሁም የወረዳ አመራሮች ከእንጦጦ ጀምሮ በቀበና ወንዝ ተፋሰስ አካባቢዎች ላይ የስራ ምልከታ አድርገዋል።

የነዋሪውን ህይወትም በሚያሻሽል መልኩ ልማቱን በማከናወን ለከተማችን ገፅታ ተጨማሪ ድምቀት ለማድረግ ነዋሪውን ያሳተፉ አበረታች እንቅስቃሴዎች መጀመራቸው በጉብኝቱ ላይ ተገልጿል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ነዋሪውን ባሳተፈ መልኩ አካባቢውን ለማልማት የተጀመሩ ቅንጅታዊ ስራዎችን በማስቀጠል አዲስ አበባን ስሟንና ግብሯን ለማገናኘት የሚደረገውን ርብርብ ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.