የከተማችን አንዱ ድምቀት የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል ውብ፣ ደማቅና ሀይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በመስቀል አደባባይ በ2,575 የተለያዩ ደብሮችና ቦታዎች ተከብሮ ተጠናቅቋል::
የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል ደማቅ ሆኖ እንዲከበር አስተዋፅዖ ያደረጋችሁ የሀይማኖት አባቶች፣ የከተማችን ወጣቶች፣ ስታስተባብሩ የነበራችሁ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች እንዲሁም ዶፍ ዝናብ ሳይበግራችሁ በዓሉ ደማቅ በሆነ መንገድ እንዲከበር ያደረጋችሁ የጸጥታ ሃይሎችና የከተማችን ነዋሪዎችን በሙሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.