ዛሬ ለኮሪደር ልማት እና ለመልሶ ማልማት ተነሺ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ለኮሪደር ልማት እና ለመልሶ ማልማት ተነሺ ነዋሪዎች የተገነቡ ምትክ ቤቶችን ተዘዋውረን ጎብኝተናል።

ለኮሪደር ልማት ተነሺዎች በመተላለፍ ላይ የሚገኙት እነዚህ የመኖሪያ ቤቶች ውሃ፣ መብራት፣ መጸዳጃ እና ማብሰያ ቦታ የተገነባላቸው፣ ለስራ እድል የሚሆኑ የመስሪያ ሼዶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የንግድ ሱቆች እንዲሁም ትምህርት ቤቶች በአቅራቢያቸው ያላቸው የመኖሪያ መንደሮች ሲሆኑ ፋርማሲዎች እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰራን እንገኛለን።

ከጎበኘናቸው የአየር ጤና እና የገላን ጉራ መንደሮች በተጨማሪ በተለያዩ የከተማችን አካባቢዎች ተመሳሳይ የመኖሪያ መንደሮችን ዝግጁ በማድረግ በልማት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ለሚነሱ ነዋሪዎቻችን በማስተላለፍ ላይ እንገኛለን።

በእነዚህ መንደሮች ከመኖሪያ ቤት በተጨማሪ ለነዋሪዎች የስራ እድል የሚሆኑ የመስሪያ ሼዶች እንዲሁም የንግድ ሱቆች የገነባን ሲሆን በመልሶ ማልማቱ ነዋሪዎች ማህበራዊ መሰረታቸው ሳይበጠስ በጋራ አንድ አካባቢ እንዲገቡም አድርገናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.