"የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በየአመቱ በልዩ ድ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በየአመቱ በልዩ ድምቀት መከበሩ አንዱ የለውጡ ፍሬ ነው"። :-አቶ አለማየሁ እጅጉ

የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በየአመቱ በልዩ ድምቀት መከበሩ አንዱ የለውጡ ፍሬ ነው። ሲሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ አስታወቁ።

በዛሬው ዕለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ፣የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱን ጨምሮ

የከተማና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች ፎሌዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት የኤሬቻ ፊስቲቫል በድምቀት ተከብሯል።

በአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ እንዳሉት የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በየአመቱ በልዩ ድምቀት መከበሩ አንዱ የለውጡ ፍሬ ነው ካሉ በኋላ በዓሉን አብሮነትንና አንድነትን የሚስያስተሳስር ስለሆነ ሁላችንም በጋራ ልናከብረውና ልንከባከበው ይገባል ብለዋል ።

አቶ አለማየሁ አክለውም በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ አካበቢ የሚመጡ ተሳታፊዎችን በምንችለው በመንከባከብ በሰላም አክብረው ወደ ሆራ አርሰዲ እስከሚሄዱ ድረስ ማገዝ አለብን።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ካባ መብራቱ በበኩላቸው በዓሉን በድምቀት ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶች መከናወናቸውን በመግለጽ እንግዶችን በፍቅር ተቀብሎ በፍቅር መሸኘት ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም በዓሉ በፍቅር በአንድነትና በጋራ መከበር እንዲችል ሁሉም አካል መረባረብ አለበት ሲሉ ገልፀዋል ።

በኢሬቻ ፌስቲቫል ላይ የኪነጥበብ ድግስ፤ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፣ የተለያዩ አካባቢዎችን የሚገልጽ አልባሳት እንዲሁም ባህላዊ የምግብ ትይንት ቀርቧል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.