
የኮሙኒኬሽን ዘርፉን በዕውቀትና በክህሎት ለመምራት ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ፤
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና የ11ዱም ክፍለ ከተማ የኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት አመራሮች በጉለለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ምልከታና ምክክር አድርጓል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትአለም መለሰ በመድረኩ እንደተናገሩት ለህዝቡ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ በማድረስ ቀዳሚ እና ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ለመሆን ዘርፉ አቅሙን እና ተደራሽነቱን ሊያሳድግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ተቀራራቢ አቅም ለመገንባት እና የኮሙኒኬሽን ስራዎችን በእወቀት እና በላቀ ቴክኖሎጂ ለመምራት እንደዚህ አይነት መድረኮች እና ልምድ ልውውጦች አስፈላጊ መሆናቸውን የጠቀሱት ወ/ሮ እናትአለም፣ የበለጠ ተቀናጅቶ ለመስራትም ያስችላል ብለዋል።
በመጨረሻም የጉለሌ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት እያስገነባ የሚገኘው ዚመናዊ ስቱዲዮ የደረሰበትን ደረጃ ምልከታ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ይህንን ተሞክሮ ወደ ሌሎች ክ/ከተሞች በማስፋት ለህዝብ የምናደርሳቸውን መረጃዎች ጥራት እና ተደራሽነትን ማሳደግ እንደሚገባ ተገልጿል። https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.