"ኢሬቻ በኦሮሞ ባህል የምስጋና ብቻ ሳይሆን ስለሠላም ፣ ስለፍቅርና ስለ አንድነት የሚሠበክበት በአል ነው!!"
፦አቶ ማሾ ኦላና
የ2017 ዓመተ ምህረት የኢሬቻ አከባበር የማጠቃለያ መርሃ ግብር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተካሄዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙባረክ ከማል ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ሲከበር ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል ይዞ የመጣ ነው ብለዋል። በተለይም በአሉ በቂርቆስ መከበር ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ የባህል ትስስር የኢኮኖሚ ዕድገትና ፍቅር አንድነት የነገሰበት ሆኗል ብለዋል።
እሬቻ ከኢትዮጵያ አልፎ በአለም የሚታወቅና ብዙ የውጭ ሀገራት ዜጎች ታድመው የሚያደምቁት ልንኮራበትና ይበልጥ ልናጎለብተው የሚገባ የመላው ኢትዮጵያውያንም መገለጫ ባህላዊ እሴታችን ያሉት አቶ ሙባረክ ይህ ኢትዮጵያውያንን በጥብቅ ቁርኝት እንዲተሳሰሩ ያደረገውን በዓላችንን መላው ኢትዮጵያውያን በመተሳሰብና በአብሮነት ይከበራል ብለዋል ።
የቂርቆስ ክፍለ ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ በበኩላቸው ኢሬቻ በተለይም የአዲስ አበባ እምብርት ለሆነችው ክፍለ ከተማ ከብዙ ጉዳዮች አንጻር ልዩ ትርጉም አለው ብለዋል። እሬቻ የሰላምና የምስጋና በዓል በመሆኑ ፍቅር ይሰበክበታል ፣ አንድነትና መተሳሰብ ጎልተው ይወጡበታል ያሉት አቶ አደፍርስ እሬቻን የምናከብረው እንሰሳቶች ሳይቦርቁ ፣አእዋፋት እንደፈለጉ ሳይበሩ፣ አራሽ ገበሬዎች የልፋታቸው ውጤት የሆነውን እሸታቸውን ከማያዩበት ወጥተው ፀሀይ ፈንጥቃ ሁሉም መሪሆ ብለው ፈጣሪያቸውን የሚያከብሩበት የብርሃን በኣል ነው ብለዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የሆረ ፊንፊኔ ማክበሪያ ማዕከል ቦታ እንደመሆኑ መጠን ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች እንደዚሁም በበአሉ ለመታደም ከሀገር ውስጥና ከውጭ የሚመጡ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ባህል ጥሩ የእንግዳ አቀባበልና መስተንግዶ ለመስጠት መዘጋጀታቸውንም ነው
በአዲስ አቧባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሾ ኦላና ኢሬቻ በኦሮሞ ባህል የምስጋና ብቻ ሳይሆን ስለፍቅር ስለሠላምና ስለአንድነት የሚሠበክበት መሆኑን ገልጸዋል።
ቂርቆስ የበአሉ አስተናጋጅ እንደመሆኑ አንድነትን አብሮነትንና ኢትዮጵያዊነትን አጠናክረን እንድንቀጥል የሚያግዘን ነው ብለዋል።
ስለሆነም የእንግዳ ተቀባይነት ባህላችንን ከፍ አድርገን
የበአሉ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የፊታችን ቅዳሜ በሆረ ፊንፊኔ እና በነጋታው እሁድ በሆረ አርሰዲ የሚከበረውን ኢሬቻ በድምቀት ለማክበር መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.