ኢሬቻ ፍቅር የሚሰበክበት በዓል በመሆኑ ይህንን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኢሬቻ ፍቅር የሚሰበክበት በዓል በመሆኑ ይህንን እሴት ማጠናከር ይገባል- አቶ ጥራቱ በየነ

ኢሬቻ ፍቅር የሚሰበክበት በዓል በመሆኑ ይህንን እሴት ማጠናከር እንደሚገባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ገለጹ፡፡

የ2017 የኢሬቻ በዓል የማጠቃለያ መድረክ በቦሌ ክፍለ ከተማ ተካሄዷል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በዓሉን ማጉላት እና ትብብርን ማሳየት ከበዓሉ ታዳሚያን ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በዓሉ ፍቅር የሚሰበክበትና በይቅርታ አብሮነት ደምቆ የሚስተዋልበት በመሆኑ ይህንን እሴት ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ አለምፀሀይ ሽፈራው፣ በዓሉ ለሀገር ግንባታ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባገዳዎች ሃደስንቄዎች እና ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.