የኢሬቻ ሳምንትን በምክንያት በማድረግ የኮልፌ ቀ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኢሬቻ ሳምንትን በምክንያት በማድረግ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፓናል ውይይት መድረክ ተካሔዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ለማ(ዶ/ር) ኢሬቻ የአንድነት የአብሮነት መገለጫ በመሆኑ ወጉንና ስርዓቱ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ መስራት እንደሚገባ ገልፀው የኢሬቻ በአል ከፊታችን ቅዳሜ እንዲሁም እሁድ የሚከበረውን የኢሬቻ በአል እንግዶችን በኢትዮጵያ እንግዳ ተቀባይነት በህላችን መሰረት መቀበል ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ባዩ ሽጉጤ በበአሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የኢሬቻ በአል የኦሮሞ ህዝብና የብሔር ብሔረሰቦች በአል ነው ሲሉ የገለፁ ሲሆን የገዳ ስርዓት ውስጥ ኢሬቻ ለፈጣሪ ትልቅ ክብር የሚሰጥና ፈጣሪ የሚመሰገንበት በአል ነው ብለዋል።

በኢሬቻ ሳምንት በአል መርሀ ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ለምስጋናና ለፍቅር ለአንድነት መገለጫ ለሆነው የኢሬቻ በአል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ኢሬቻ የተጣላ የሚታረቅበት ቂምና ጥላቻ ሳይኖር በጋራ የሚከበር በአል ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም የገዳ እና የሞጋሳ መገለጫ የሆነው ኢሬቻ ወደ ትውልዱ ማስተላለፍ እንደሚገባ ገልፀው ኢሬቻ ለኢኮኖሚ ትልቅ ፋይዳ ያለው በአል ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ በበኩላቸው እንኳን ለ2017 የኢሬቻ በዓል ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ በማለት የኦሮሞ ህዝብ የራሱ የሆነ ባህል ያለው ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የገዳ ስርዓት አንዱ ነው ብሏል።

አቶ ሙልጌታ በመልእክታቸው የኢሬቻ በአልን በወንድማማችነት እሴት ከኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በጋራ በማክበር አብሮነትን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል ።

 

 

 

 

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.