ዛሬ የ2017 በጀት ዓመት የከተማ አቀፍ የገቢ ንቅናቄ መድረክ በማዘጋጅት ከግብር ከፋዮቻችን እና ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገናል::
በውይይት መድረኩ ላይ ግብር ከፋዮቻችን በከፈሉት ግብር የተሰሩ ስራዎችን አድንቀው ቢስተካከሉ የሚሏቸው ክፍተቶችን ያስረዱን ሲሆን በግብር ከፋዩች በኩልም ሊስተካከል የሚገባውን ዘርዝረው አንስተዋል::
ግብር ከፋይና ግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤቶች ቤተሰቦች በመሆናቸው በጋራ ፣ በትብብር መስራታችንን ይበልጥ በማጠናከር ሀገርን መገንባታችንን እንቀጥላለን:: ያለ ግብር ፍትሃዊነት እንዲሁም ያለ ግብር መሰረተ ልማት አይጠበቅምና ይህ የጋራ ጉዳያችን በመሆኑ ግብር ከፋዮቻችን ግብራቸውን በወቅቱ በፍቃደኝነት በመክፈል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እንዲሁም ጉቦ የሚቀበሉ አካላትን በማጋለጥ እና መብታቸውን አውቀው እንዲታገሉ ጥሪ አቀርባለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እናህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.