የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚያከናውነው የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚያከናውነው የኮሪደር ልማት ከአራዳ ክ/ከተማ ለሚነሱ ነዋሪዎች ምትክ የጋራ መኖሪ ቤት እጣ ማውጣት ተካሄደ፤

የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ዙሪያ ከሚገኙ የአራዳ ክ/ከተማ አካባቢዎች በምርጫቸው መሰረት የጋራ መኖሪያ ቤት አማራጭ ተጠቃሚ ለመሆን የፈለጉ 402 ነዋሪዎች የመጀመሪያ ዙር ኮንዶሚኒየም እጣ ማውጣት ፕሮግራም ተካሂዷል።

ዛሬ ዕጣ የማውጣት ፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉት አዲስ አበባን በተለይ ፒያሳና አካባቢዋን የሚመጥን የኮሪደር ልማት ስራ የሚሰራባቸው አካባቢዎች ላይ የሚኖሩሚገኙ ተነሺዎች ሲሆኑ፣ የልማት ተነሺዎቹ በምርጫቸው መሰረት ተገቢው ምትክ እኔደሚሰጣቸው በተገባው ቃል መሰረት ዛሬ የኮንዶሚኒየም እጣ ማውጣታቸው ታውቋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.