“ኢሬቻ ለህዝባችን ትስስርና ወንድማማችነት የሚኖ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ኢሬቻ ለህዝባችን ትስስርና ወንድማማችነት የሚኖረው አስተዋጽኦ የጎላ ነው!” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

6ኛው የኢሬቻ ፎረም "ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ"በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ በአድዋ ድል መታሰቢያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል።

በፎረሙ ላይ የመከፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት፡- የህዝባችን አብሮነት፣ አብሮ መኖርንና መተባበርን መሰረት ካስያዙ ባህሎች መካከል ኢሬቻ አንዱ ነው፡፡

ኢሬቻ ከባህላዊ ክንውን አልፎ ለከተማችን እና ለሃገራችን የቱሪዝም መስህብ እየሆነ መጥቷል፡፡ የበለጠ ካስተዋወቅነው እና ጎልቶ እንዲታይ ካደረግነው  ከዚህ በላይ የቱሪዝም መስህብነቱ የሚጨምር እንደሚሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።

በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ኢሬቻ ፍቅር ነው፣ ኢሬቻ አብሮነት ነው፣ ኢሬቻ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለህዝባችን ትስስርና ወንድማማችነት የሚኖረው አስተዋጽኦ የጎላ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.