ኢሬቻ የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድበን በጋራ የምናከብረው የአንድነት ምልክታችን ነው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ
“ኢሬቻ የሃይማኖት ልዩነት ሳይገድበን በጋራ የምናከብረው የአንድነት ምልክታችን ነው” ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።
በ6ኛ የኢሬቻ ፎረም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት አቶ ሽመልስ፣ “ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እንዲሁም የጎረቤት ሀገራት በዓል እየሆነ መጥቷል” ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ገንቢ የሆኑ የኦሮሞ ባህላዊ እሴቶችን የመንግሥት የአስተዳደር አካል እያደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ከእነዚሀ መካከል ባህላዊ ፍርድ ቤቶች እና የዜግነት ግዴታ የሆነውን የእርስ በርስ መተጋገዝ "ቡሳ ጎንፋን" ሥራ ላይ እያዋለ መሆኑን ነው የጠቆሙት።
ሕፃናት ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ግብረ ገብነትን እንዲማሩ የገዳ ሥርዓትን የሥርዓተ-ትምህርት አካል ተደርጎ እየተሰጠ ይገኛልም ብለዋል።
ኢሬቻ የመሻገር በዓል ነው ያሉት አቶ ሽመልስ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ፈጣሪው (ዋቃ) ስላደረገለት መልካም ነገር ሁሉ የሚያመሰግንበት እንዲሁም መጪው ጊዜ መልካም እንዲሆን ለፈጣሪው አደራ የሚሰጥበት ልዩ በዓል መሆኑን በንግግራቸው ጠቁመዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.