እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

የኢሬቻ በዓል የክረምቱ ጭጋግ አልፎ ብራ ሲሆን፣ ወንዞች ጎድለው  ምድር አረንጓዴ ለብሳ በአበቦች ስትዋብ፣ ቡቃያው ደረስኩ ደረስኩ ሲል፣ ክረምቱ ወደ ጸደይ ሲሸጋገር ተለያይቶ የቆየው ሁሉ የሚገናኝበት የአንድነት እና የወንድማማችነት መገለጫ በዓል  ነዉ።
ኢሬቻ የገዳ ስርዓት አንዱ ምሰሶ  ሲሆን የምስጋና፣ የአንድነት፣ የሰላም፣ የእርቅ እና የይቅርታ ተምሳሌት፣  የተራራቀ የሚገናኝበት  በዓል ነዉ ።

በብዝሃነት አጊጣ፣ በበጎነት ተኩላ፣ በትጉህ እጆች ያበበችው የሁላችን ጎጆ አዲስ አበባ እንግዶቿን በተለመደው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ተቀብላ  እያስተናገደች የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ቱሪስቶችን የምትስብ የጋራ መድመቂያ ከተማችን ሆናለች።

ዉድ  የከተማችን ነዋሪዎች፤  ከተማችንን ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል፣ የቱሪስት መዳረሻ ካደረጓት የአደባባይ በዓላት መካከል አንዱ የኢሬቻ በዓል  በመሆኑ ለህዝብ ትስስር፣ አብሮነት እና  ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የላቀ ሚና እንዳለው በመረዳት እንግዶችን ተቀብላችሁ በማስተናገድ አብሮነትን እና ወንድማማችነትን ከፍ ስላደረጋችሁ በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ!

መልካም በዓል!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.