በ2016 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል መልቀቂ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በ2016 የትምህርት ዘመን በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ 500 እና ከዚያ በላይ የሆነ ውጤት ያስመዘገቡ 484 የከተማችን ተማሪዎችን ሸልመን አበረታተናል።

ትምህርት የእድገት ሁሉ መሰረት መሆኑን ተገንዝበን በትምህርት ስርዓታችን ላይ የተፈጠረውን ስብራት ለመጠገን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ ከአምናው በ 5% እድገት ያሳየ ውጤት አስመዝግበናል።በዚህም በሀገር አቀፍ እና በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን እና አመራሮችን አመስግነን እውቅና ሰጥተናል።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ከፍተኛ ዉጤት ባስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ፤

1ኛ ከፍተኛ ዉጤት - 575 ባስመዘገበችው ተማሪ ሲፈን ተክሉ፣

2ኛ ውጤት - 573 ባስመዘገቡት ተማሪ ማዕዶት እስክንድር እና ተማሪ ሶሊያና ሀብታሙ

3ኛ ውጤት - 570 ባስመዘገበችው ተማሪ ያስሚን ከድር

እጅግ የኮራን ሲሆን ከተበረከተላቸው እውቅና እና ሽልማት በተጨማሪ የውጭ ሀገር የትምህርት እድል(Scholarship) ሽልማት አበርክተንላቸዋል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.