የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል::
የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ በዘመቻ መልክ እንደሚካሄድ ተገለፀ።
በፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ትግበራ ዙሪያ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዛሬ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
በዚህም ሁለቱ ተቋማት የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ትግበራውን በጋራ እንደሚመሩት አስታውቀዋል።
የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባው በአዲስ አበባ ከነገ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኤጀንሲው 119 የወረዳ እና 11 የክፍለ ከተማ ቅርንጫፎች እንደሚካሄድ ተቋማቱ ገልፀዋል።
የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟሉ የሀገሪቱ ነዋሪዎች የሚሰጥ ባለ 12 አኀዝ ልዩ መለያ ቁጥር ነው።
አገልግሎቱ ያለምንም ክፍያ በነፃ እንደሚሰጥም ተቋማቱ ገልፀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.