በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛ ዙር የአ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛ ዙር የአመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች 'የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት'' በሚል መሪ ሀሳብ ሁለተኛ ዙር የአመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል፡፡

በዚህ ሁለተኛ ዙር ስልጠና በአዲስ አበባ ደረጃ ከ2400 በላይ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የሚሳተፉ ሲሆን ፥ ስልጠናው በሚቀጥሉት 10 ቀናት የሚሰጥ እንደሆነም ታውቋል።

በንድፈ ሀሳብና በነባራዊ እውነታዎች ተደግፎ በሚሰጠው በዚህ ስልጠና በየደረጃው ያለው አመራር ዓለም አቀፋዊ ፣ አህጉራዊ፣ ቀጣናዊና ሀገራዊ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ ወቅቱን የዋጀና ውጤታማ አመራር ለመስጠት የሚያስችለው መሆኑን በስልጠናው ዙርያ ማብራርያ እና አቅጣጫ ያስቀመጡት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገልጸዋል፡፡

አመራሩ ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ለቀጣይ የልማት ስራዎች በተሻለ ደረጃ ራሱን እንዲያዘጋጅ ማሳሰባቸውን ከብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ስልጠናው ሀገሪቱ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ከግብ ለማድረስ አመራሩ በአስተሰሰብ ፣ በእውቀት፣ በክህሎትና በሥነ ምግባር ጎልብቶ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃትና በቁርጠኝነት ለመወጣት የሚያስችለውን አቅም ያዳብራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልፀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.