ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ያገኝነውን መረጃ እናጋራችሁ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 ንዑስ አንቀፅ 9 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሚፈለግባቸውን የታክስ ( ግብር ) ዕዳ በሕግ በተቀመጠው ጊዜ ባለመክፈላቸው ምክንያት የታክስ ባለዕዳዎች በህግ ሀብት /ንብረት በመያዝ ላልተከፈለው ዕዳ ማካካሻነት እንዲሆን ይደነግጋል ።
በህጉ መሠረት በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ በመመሪያ 6/2011 መሠረት ቅዳሜ መስከረም 18 /2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ መሰረት
የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ብዛታቸው 13 ፣
ለመኖሪያ የሚያገለግል ኮንደሚኒየም ባለ ሁለት መኝታ ቤት አንድ ፣
ባሉበት ሁኔታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለእያንዳንዱ ንብረት በተገለፀው የዋጋ መነሻ መሠረት አጫርቶ ለመሸጥ ይፈልጋል ።
ከመስከረም 18 እስከ ጥቅምት 4 : 2017 ዓ. ም. እስከ ጠዋቱ 4፡00 ድረስ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን ።
ማሳሰቢያ ፦ ጨረታው ጥቅምት 04 ቀን 2017 ዓ/ም ከጧቱ 4:30 ተዘግቶ ከጠዋቱ 4:45 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ፤
የመኖሪያ ቤት ጨረታው እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ/ም 4:30 ድረስ የሚቆይ እና ጨረታውም በዛው ቀን 4 :45 የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
#ለበለጠ_ዝርዝር _መረጃ ፦ ቅዳሜ መስከረም 18 /2017 ዓ.ም በወጣው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ መመልከት ትችላላችሁ ፤ እንዲሁም በዋና መሥሪያ ቤት 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 001 በታክስ ዕዳ በተያዙ ንብረቶች አስተዳደር እና ሽያጭ ቡድን ዝርዝር መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ
ግብር ፣ ለሀገር ክብር !
ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ፣ ለአዲስ አበባ ብልፅግና !
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.