6ኛው የሚላን የከተሞች የምገባ ፖሊሲ ፎረም በአ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

6ኛው የሚላን የከተሞች የምገባ ፖሊሲ ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።

6ኛው የ2024 የሚላን የከተሞች የምገባ ፖሊሲ ፎረም "የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ለጤናማ እና ቀጣይነት ለላለው የአፍሪካ ከተምች እድገት!" በሚል መሪ ቃል በተከታታይ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመዲናዋ እየተካሄደ ባለው የሚላን የከተምች የምገባ ፎረም ላይ ከ40 የአፍሪካ አባል ከተሞች፣ የሚላን የከተሞች የምገባ ፖሊስ ፓክት አስተባባሪዎች ፣በተባበሩት መንግስታት የአለም የምግብ ፕሮግራም ተወካይ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አባሳደር እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በመድረኩ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሲ፣ከተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች የተወጣጡ አመራሮች እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በፎረሙ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አዲስ አበባ ከተማ ፎረሙን እንድታዘጋጅ የተመረጠችው በፈረንጆቹ 2022 በብራዚል ሬውድጄነሮ ከተማ በትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም የምርጥ ተሞክሮ ዓለም አቀፍ የሞዴል እውቅና እና ሽልማት ያገኘች መሆኑን ተከትሎ ነው ብለዋል።

እንደ ምክትል ከንቲባው ማብራሪያ በአዲስ አበባ ከተማ በ255 ትምህርት ቤቶች ከ801 ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ የተደረጉ ሲሆን በዚህም ከ16 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል።

በተመሳሳይ በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በመዲናዋ ከ36 ሺህ በላይ አረጋውያን የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን በማስመልከት ምክትል ከንቲባው ለፎረሙ ተሳታፊዎች ያላቸው ተሞክሮ አካፍለዋል።

በኢትዮጵያ የጣሊያን አባሳደር አውጎስቲኖ ፓሊስ በበኩላቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደውን የትምህርት ቤቶች እና የማህበረሰብ የምገባ ፕሮግራም አድንቀው የሚላን የከተሞች የምገባ ፖሊሲን ለማጠናከር በጋራ ለመስራት ዝግጅ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

አዲስ አበባ የሚላን የከተሞች የምገባ ፓሊስ ፓክት በይፋ አባል ሁና የተቀላቀለችው በፈረንጆቹ 2021 ሲሆን 233 የዓለም ከተሞች የፎረሙ አባል ናቸው።

ለ2 ቀናት የሚቆየው 6ተኛው ቀጠናዊ የMilan Urban Food Policy Pact Forum በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.