በቅድሚያ የረዳን ፈጣሪ ይመስገን እንኳን ደስ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በቅድሚያ የረዳን ፈጣሪ ይመስገን እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ,!

በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ የ2024 ስማርት ሲቲ ሊደርሺፕ ሽልማት ከ72 ሀገሮችን እና ከ115 አቻ ከተሞች አስተዳደር ከንቲባዎች መካከል ምርጥ የአመራር ሸልማት በማግኘታችን በከተማ አስተዳደሩ ስም እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ይህ ያስመዘገብነው ውጤት በከተማችን በተሰሩ እና በህዝባችን ተሳትፎ እና ቅንጅት የተገኘ ውጤት በመሆኑ ለዚህ ወጤት መገኘት አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላትን ሁሉ እያመሰገንኩ፣ በደቡብ ኮሪያ 2024 ሴኡል ስማርት ሲቲ ሊደርሺፕ የእውቅና ሸልማት ስለተበረከተልንም እናመሰግናለን።

ለህዝባችን ሰርተን በምናገኘው እውቅና ሁሉ ተመስጋኙ ሁሌም ከጎናችን በመሆን የልማቱ ዘዋሪ እና ተጠቃሚ የሆናችሁ የከተማችን ነዋሪዎች መሆናችሁን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።

በድጋሚ እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባረክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.