ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ባለችው እመርታየአፍሪካ ምርምር እና ኢንተለጀንስ አገልግሎቶች ተቋም (IOA/አይኦኤ) የምግብ ዋስትና ካረጋገጡ ምርጥ የአፍሪካ ሀገሮች መካከል ከደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ መያዟን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት ደቡብ አፍሪካ 94 ነጥብ 22 በመቶ የምግብ ዋስትናዋን በማረጋገጥ ቀዳሚ ሀገር ስትሆን ኢትዮጵያ 91 ነጥብ 31 በመቶ በማሳካት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡
ኢትዮጵያ ባለፈው በጀት ዓመት 8 ነጥብ 1 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቧ ይታወሳል።
ሞሮኮ፣ አልጀሪያ፣ ናይጀሪያ፣ ጋቦን፣ ርዋንዳ፣ ጋና፣ ሴኔጋል እና ናሚቢያ ደግሞ በቅደም ተከተል ደረጃ መያዛቸውም የተቋሙ ሪፖርት ያረጋግጣል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.