አዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ከከተማ አስተዳደር እና የፌዴራል ተቋማት የተወጣጡ የሁለተኛ ዙር "የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት!!" ሰልጣኝ አመራሮች በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው ።

በጉብኝታቸውም የሜክሲኮ ፣ሳር ቤት፣ ወሎ ሰፈር፣ ቦሌ እና ሌሎች በኮሊደሩ የለሙ ቦታዎችን እና የአቃቂ የግብርና ማቀነባበርያ ፣ የነገዋ የሴቶች ተሀድሶ ማዕከል ፣ የልበ ብርሀን ማዕከል ፣ የተቀናጀ የከተማ ግብርና ፣ የእንጀራ ፋብሪካዎች ፣ የነዋሪዎች ምዝገባ እና መረጃ ማዕከል፣ የከተማችን የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፣ እና ሌሎች የፌዴራል ተቋማትን ተመልክተዋል።

በተለይም ባለፉት ጥቂት ወራት የተሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የተናገሩት የጉብኝቱ ተሳታፊ አመራሮቹ ይህም ገፅታን ከመቀየሩ በተጨማሪም የህብረተሰቡን ህይወት ያቃለሉ ስለመሆናቸውም ገልፀዋል።

አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ከመሆኗም ባሻገር የብዙ ዲፕሎማቶች መዳረሻ ናት ያሉት የጉብኝቱ ተሳታፊዎች አሁን የተሰሩ ስራዎች ከተማዋን የሚመጥኑ ስለመሆናቸውም አንስተዋል።

በፕሮጀክቶቹ ግንባታ በሳል አመራር የታየ መሆኑን ያነሱ ሲሆን ለዚህ እውን መሆን ድርሻቸው ለጎላው የከተማዋ አመራሮች ምሰጋናም አቅርበዋል።

በተጨማሪም ስልጠናው የአመራር ብቃትን እንድናዳብር እና በቀጣይ የስራ ዘመን ተሞክሮ እንድንወስድ ያደረገ ነው ያሉት የጉብኝቱ ተሳታፊዎች የዛሬው ጉብኝት ደግሞ ይህን በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል።

በመዲናዋ የታየው ፈጣን ለውጥ የአመራሩን ቁርጠኝነት እና የማህበረሰቡን ተሳትፎ የሚያሳይ ነው ያሉን አመራሮቹ ይህም በቀጣይ ስራችን ተሞክሮ እና ስንቅ ሆኖ ያገለግላል ሲሉ ተናግረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.