ከሁለተኛ ዙር “የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት!” ሰልጣኝ አመራሮች ጋር በመሆን በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች፣ በተለይም በፌደራል ፖሊስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመገኘት በተቋም ግንባታና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ የተሰሩ አስደማሚ እና ዘመኑን የዋጁ ስራዎችን ጎብኝተናል።
እንደነዚህ ያሉ በቴክኖሎጂ የተደራጁ ተቋማትን መገንባት የበለጸገችና ተወዳዳሪ የሆነች ኢትዮጵያን ለማረጋገጥ፣ ከተማችንን ስማርት ስቲ ለማድረግ እንዲሁም የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ በኩል ትልቅ አቅም የሚሆኑ ሲሆን እያበረከታችሁት ላለው አስተዋፅዖ ሁሉ በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.