17ተኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ- ዓላማ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተከበረ፡፡
7ተኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችን፤ለሉአላዊነትነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተከብሯል፡፡
በበዓሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ -ጉባኤ ወ/ሮ ፋይዛ መሐመድ፣ የከተማችን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ጠሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመርሀ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ -ጉባኤ ወ/ሮ ፋይዛ መሐመድ :- የህዝባዊ አንድነታችንና የህብረ -ብሔራዊነታችን መገለጫ የሆነውን የሰንደቅ ዓላማችን ቀን ስናከብር በብልጽግናችን የጋራ መግባበት በመፍጠር ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን እና ሀገራዊ አንድነትን በማጽናት መሆን አለበት ብለዋል።
ሰንደቅ ዓላማ ከምልክትነትም ባሻገር ህልውናችን ነው ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ የአሁኑ ትውልድ መንግሥት የጀመራቸውን የላቀ ሀገራዊ ትርጉም ያላቸውን ስራዎች በሚችለው በመደገፍና የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በማስቀጠል በልማቱ መስክ አዲስ የጋራ ታሪክ በመጻፍ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.