ዛሬ ከመሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ከመሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ጋር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የሪፎርም እና የዲጂታላይዜሽን ስራን ጎብኝተናል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅድሚያ ትኩረት የሰጣቸውን 16 ከፍተኛ የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለይቶ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ የሪፎርም እና የተቋም ግንባታ ስራ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል። ከነዚህ ተቋማት መካከል የመሬት ልማት አገልግሎትን ፈጣን፣ ተደራሽ፣ ጥራት ያለው እንዲሁም ዲጂታላይዝ በማድረግ በኩል የጀመርነዉ ስራ ውጤታማ መሆኑን አይተናል።

በተለይም እስከ ዛሬ ድረስ የተፈጠሩ መብቶችን ወደ ዲጂታል የመቀየር፣ አዳዲስ የተፈጠሩ መብቶችን በግልፅነትና በታወቀ ውሳኔ ብቻ መብት እዲፈጠር የማድረግ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ፋይል በፎርጂድ ተደራጅቶ ሲመጣ ወደ ሲስተም እንዳይገባ የመከላከል፣ በተጭበረበረ እና በህገወጥ መንገድ መብት ፈጠራን የመለየት፣ በህገ ወጥ መንገድ መብት ቢፈጠር እንኳን በቀላሉ ውድቅ የሚሆንበት፣ ለጀርባ ማህተም ተገልጋይ የማይንገላታበት፣ የደብዳቤዎች ስወራን እንዲሁም ከሰው ማህደር ውስጥ ፋይል ማጥፋትና በህገወጥ መንገድ ፋይል የመጨመር እና ተገቢ ያልሆነ ጥቅምን በሚያስቀር ደረጃ የተሟላ የዲጂታል ስራ እየተተገበረ ይገኛል።

ስለዚህ ውድ ተገልጋዮቻችን ይህ ከፍተኛ እንግልት የነበረበት አገልግሎት፣ እንግልቱ ቀንሶ ዉሳኔ የሚያስፈልገዉ ካልሆነ በስተቀር በያላችሁበት ቦታ ሆናችሁ መገልገል የምትችሉበትን ስርዓት የዘረጋን ሲሆን አገልግሎቱን በመረዳት በህጋዊ መንገድ መገልገል የምትችሉ መሆኑን እገልጻለሁ።

አገልግሎቱን ከዚህ በላይ የላቀ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሲስተሙን እኩል መጠቀም እንዲችሉ እነሱንም የማናበብ ስራ እየሰራን የምንገኝ ሲሆን አሁን የሊዝና የመሬት አገልግሎት ክፍያን ጨምሮ ሁሉም ክፍያዎች ግለሰብ ጋር ሳይደርስ በባንክ እና ቴሌብር በኩል እንዲከፈል ማድረግ ስለተቻለ ተገልገሉበት።

ይህንን መልካም ጅማሮ ተደራሽ ለማድረግ ይበልጥ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.