ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም አክስዮን ለሽያጭ ዝግጁ መሆኑን ያበሰርንበት የታሪካዊ ክንውን ምዕራፍ እለት ነው። ባለፉት ስድስት አመታት ከፖለቲካዊ አብዮት ወደ የለውጥ መንገድ እያደረግነው ያለነው ስኬታማ ጉዞም ማሳያ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
እንደ ዲጂታል ኢትዮጵያ ያሉ ቁልፍ የለውጥ ሥራዎች መተግበራቸው ለዛሬው ታሪካዊ ሁነት ፅኑ መደላድል ፈጥረዋል። በተለያዩ ዘርፎችም የሚታይ እድገትን አስችለዋል። 50 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የገንዘብ ዝውውር ተግባራቸውን በሞባይል እንደማከናወናቸው የ130 አመታት ዕድሜ ባለፀጋው ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክስዮን ድርሻውን በሽያጭ ለሕዝብ አቅርቧል። ይህ ለኢትዮጵያ የአክስዮን ገበያ መደላድል የሚፈጥር ብሎም በሀገራችን ካሉ ቀዳሚ መንግሥታዊ የንግድ ተቋማት( አሁን ወደ አክስዮን ድርጅትነት የተለወጠ) አንዱ ከሆነው ከአንጋፋው ኢትዮ ቴሌኮም የባለቤትነት እድልን የሚያሰፋ ክንዋኔ ነው። ሁላችንም እንኳን ደስ አለን!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.