እንኳን ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ! የክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት
“ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት በድምቀት አክብረናል።
የሴቶችን መብትና የፆታ እኩልነት በማረጋገጥ በሃገራችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የልማት ተሳትፎዎች ላይ ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግ በሁሉም ዘርፍ እየሰራን ነው።
እስከአሁን ብዙ ጥረት ሲደረግ ቢቆይም፣ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና እኩል ተሳታፊነት ማረጋገጥ ብዙ ክፍተት ስላለበት ተጨማሪ ጥረትና ስራ ይፈልጋል።
ይህን ክፍተት ማጥበብ ደግሞ ከማንም በላይ እድሉን አግኝተን ሀገር እየመራን ካለነው ሴት የፖለቲካ አመራሮች ይጠበቃል።
እኛ በየተሰማራንበት ውጤታማ ከመሆን አልፈን እድሉን ላላገኙ ሴቶች ምሣሌዎች፣ በር ከፋቾች፣ ማበረታቻዎችና እንደሚችሉ ማሳመኛ መረጃና ማስረጃዎች መሆን እንችላለን።
ከዚህም አልፎ የሴቶች ተጠቃሚነትንና ሁለንተናዊ ተሳትፎን ለማረጋገጥ የሚችሉ ተጨባጭ ስራዎችን የመስራት ኃላፊነት አለብን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ለበለጠ መረጃ
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.