ከተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች፣ ከከተማችን ነዋሪዎችና ከልማት ተነሺዎች ተወካዮች፣ ከታዋቂ ሰዎች እና ከሐይማኖት አባቶች ጋር በኮሪደር ልማት ሥራ ሂደት ላይ ጥልቅ ውይይት አድርገናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በውይይቱ ከኮሪደር ልማት አስፈላጊነት ጋር ተያይዞ ያሉ ጥንካሬዎች፤ እጥረቶች፣ ሃሜቶች ሳይቀሩ የተለያዩ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች በዝርዝር ተነስተዋል።
እኛም ከልማት እና የህዝብን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ዉጪ ምንም ድብቅ አጀንዳ ስለሌለን ሁሉንም መረጃ እና አሰራር በዝርዝር አቅርበን ግንዛቤያቸውን የሚጨምሩ እና የመረጃ ክፍተቶችን የሚሞሉ እንዲሁም ላነሱዋቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሚሆኑ ማብራሪያዎች ሰጥተናል።
ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ በሚነሡ የተዛቡ መረጃዎች ላይም ግልፅነት ፈጥረናል። ካዋረደን የድህነት አረንቋ ውስጥ ለመውጣት ቆርጠን እየሰራን እና ያረጁ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ቤቶችን እየቀየርን የዜግነት ክብርን ማረጋገጥ ላይ ስለመሆናችን የግንዛቤ ችግር ባይኖርም፣ የልማት ፍላጎቱ ግን ዕለት በዕለት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን መገንዘብ ችለናል።
የለዉጥ መንገድ አልጋ በአልጋ ስለማይሆን ጊዜያዊ ችግሮችን ተቋቁመን መሰረታዊ ለወጥ ለማምጣት በጋራ መትጋት እንዳለብን ተግባብተናል።
ከምንም በላይ የከተማችንን ነዋሪዎች ልናመስግናቸው ይገባል። አስፈላጊነቱን በመገዘብ ለልማት የሚያስፈልገውን ትብብር ሁሉ በማድረግ ከጎናችን መሆናቸውን አይተናል። እኛም ለማገልገል ቆርጠን ነው የገባንበት።
ለዚህም ለከተማችን ብልፅግና ያለ እረፍት በፍጥነት መስራታችንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆናችንን ለማረጋግጥ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.