ከተማችንን ወደ አምራችነት በማሸጋገርና የምርት አቅርቦትን በማሻሻል የገበያ መረጋጋት ከፈጠርንባቸው ስራዎቻችን መካከል በ14 ሔክታር መሬት ላይ የገነባነው የእንስሳት ልማት እና የልህቀት ማዕከል ስራችን አንዱ ነው::
ዛሬ ባደረግኩት ጉብኝት ማዕከሉ የመቻላችንና የውጤታማነታችን ማሳያ በመሆን ለከተማችን ነዋሪዎች ጥራት ያላቸው ምርቶችን ከማቅረብ በተጨማሪ ለበርካቶች የስራ እድልን የፈጠረ እና ለአካባቢው አርሶ አደሮች የቴክኖሎጂ ሽግግርን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን በመመልከቴ እጅግ ደስ ብሎኛል::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.