"ለነዋሪዎቿ ምቹና ውበ ከተማ አዲስ አበባ"!
የቦሌ ኤርፖርት መገናኛ የኮሪደር ልማት መንገድ አሁናዊ ገጽታ
በከተማችን አዲስ አበባ በመጀመሪያዉ ዙር ከተገነቡ የኮሪደር ልማት የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የቦሌ ኤርፖርት መገናኛ አደባባይ ኮሪደር ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶች የሚያልፉበት ዋነኛ መንገድ ነው፡፡
ይህ ሰፊ የትራፊክ እንቅስቃሴ የሚካሄድበት የኮሪደር ልማት የመንገድ ፕሮጀክት ምቹ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዲኖር በሚያስችል መልኩ የተገነባ፤ለዕይታ ማራኪ የሆኑ የመንገድ ዳር ግንባታዎችና አገልግሎት መስጫዎችን ያካተተ እንዲሁም ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ የዋሉበት ሆኖ የተጠናቀቀ በመሆኑ የከተማችንን ብሎም የክፍለ ከተማችንን ገጽታ ሳቢና ማራኪ ከማድረግ አኳያ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ እንደሆነ ይታመናል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.