"ስልጠናው ህልሞቻችንን ለማሳካት የአስተሳሰብ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ስልጠናው ህልሞቻችንን ለማሳካት የአስተሳሰብ ለውጥ አምጥቷል ፤ ተጨማሪ አቅምም ፈጥሯል!!" : - አቶ ሞገስ ባልቻ

"የህልም ጉልበት ለእመርታዊ ዕድገት " በሚል ርዕስ በከተማችን በየደረጃው ለሚገኙ ሶስተኛ ዙር ሰልጣኝ አመራሮች ሲጠጥ የቆየው ስልጠና የጋራ ተግባቦት እና ከፍ ያለ ተነሳሽነት በመፍጠር ተጠቃሏል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ያሏትን ብዙ አቅሞች ተጠቅማ እመርታዊ ድሎችን እንድታስመዘግብ የተያዙ ህልሞችን ለማሳካት ስልጠናው የአስተሳሰብ ለውጥ እና ተጨማሪ አቅም ፈጥሯል ብለዋል።

በተመዘገቡ ስኬቶችና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተግባቦት ለመፍጠር እንዲሁም በሀገራዊ ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የተሟላ እይታ እንዲያዝ ማስችሉን ያመላከቱት አቶ ሞገስ በአመራሩ መካከል የነበሩ የአፈፃፀም ልዩነቶችን በማጥበብ የከተማችንን ፈጣን ዕድገት ለማስቀጠልና የህዝባችንን አዳጊ ፍላጎት ለማሟላት ተነሳሽነትን ከፍ ማድረጉንም አስገንዝበዋል።

ህብረ ብሔራዊቷን ከተማችንን የሚመስል ማንነት ላለው አመራራችን መሰል ስልጠናዎች የአመለካከት አንድነትን ከማጠናከራቸው ባለፈ እርስ በእርስ እንዲማማርና ተሞክሮውን እንዲለዋወጥ ማስቻላቸውንም ከዚህ በፊት የተሰጡ ስልጠናዎች ያስገኙትን ውጤትም በማጣቀስ አብራርተዋል።

የፓርቲያችንን ጥልቅ እሳቤዎች በተግባር በመተርጎም የህዝባችን ህይወት ለማሻሻልና ሁለንተናዊ ብልፅግናችንን ለማረጋገጥ ተቋማትን በፅኑ መሰረት ላይ መገንባት ወሳኝ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው ለዚህም የአመራሩ ቁርጠኝነትና መልካም ስነ ምግባር የተላበሰ አገልጋይነት ይበልጥ ሊጎለብት እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሰልጣኝ አመራሮች በጥብቅ ዲስፕሊን እና በነቃ ተሳትፎ መከታተላቸውን የገለፁት አቶ ሞገስ ስልጠናው በስኬት እንዲጠናቀቅ በማስተባበሩ ፣ በሰላምና ፀጥታ ስራዎች እንዲሁም በሌሎችም ተግባራት የተባበሩ አካላትንም አመስግነዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.