ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር መርህን በመከተል ማህ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር መርህን በመከተል ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎችን እየሰራ ነው- አቶ አለማየሁ እጅጉ

ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር መርህን በመከተል ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ገለጹ፡፡

በልደታ ክ/ከተማ "የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልና የአባላት ስልጠና ፕሮግራም እየተካሄደ ነው።

በፕሮግራሙ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ፣ ብልፅግና ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጠናከር ህብረ ብሄራዊነትን በተግባር ማረጋገጥ የቻለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ፓርቲው ባለፍት 5 ዓመታት ሰው ተኮር ተግባራትን በመከወን የዜጎችን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በዚህም አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን፣ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ሰርቶ በማጠናቀቅ ፣ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን በመተግበር፣ ሰላምን በማረጋገጥ፣ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በመከወን፣ በርካታ የስራ እድል በመፍጠርና ሌሎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በመስራት ዜጎችን ተጠቃሚ አድርጓል ሲሉ ገልፀዋል።

በቀጣይ እስካሁን ከተመዘገቡ ውጤቶች የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ከልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.