ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሠራተኞቹ የሚያሰራቸውን የ5ሺህ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ አስጀምረናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
እንዲሁም ሰንሻይን ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማሕበር፣ መንግስት ከስድስት ዓመታት በፊት በነጻ ባስረከበው 3.8 ሄክታር መሬት ላይ ያስገነባቸውን 5ሺህ ቤቶች መርቀናል።
የህዝባችን ዋነኛ ችግር የሆነውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል አንዱ አማራጭ የግል አልሚዎችን ማበረታታትና በአጋርነት የምንሰራበትን ሁኔታ ማመቻቸት ሲሆን፣ የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ በሁሉም አማራጮች እየሰራን እንገኛለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.