ከንቲባ አዳነች አቤቤ ካዛንቺስ አካባቢ ካሉ ባለ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ካዛንቺስ አካባቢ ካሉ ባለሀብቶች ጋር አካባቢውን በትብብር መልሶ ማልማት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል::

በውይይቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለማድረግ በተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ እንደ መጀመሪያው ሁሉ የሁለተኛውንም የኮሪደር ልማት ስራ ህብረተሰቡን እና ባለሀብቱን በማሳተፍ በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል::

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የካዛንቺስ አካባቢ ባለሀብቶች በበኩላቸው በኮሪደር ልማት እና በመልሶ ማልማት ስራው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን የከተማው ጽዳትና ውበት ለኢኮኖሚ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ በመሆኑ በሚችሉት ሁሉ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም አካባቢውን እንደሚያለሙ ቃል በመግባት እንዲሁም ያላቸውን የልማት ጥያቄዎች በማቅረብ ለመልሶ ማልማት ስራው በቀረበላቸው ጥሪ ደስተኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.