ዛሬ ማለዳ ከቦሌ ካርጎ እስከ ቡልቡላ አቃቂ ድል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ማለዳ ከቦሌ ካርጎ እስከ ቡልቡላ አቃቂ ድልድይ ድረስ ተገንብተው ለነዋሪዎቻችን አገልግሎት ክፍት የተደረጉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ጎብኝተናል።

በቦሌ ክፍለከተማ እየተገነባ ያለውን 13 ኪ.ሜ የሚሸፍን የአረንጓዴ ልማት ስራ ተዘዋውረን የጎበኘን ሲሆን ይህም አራት ዘመናዊ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች፣ ሁለት የህጻናት የመጫዎቻ ሜዳዎች፣ አንድ የስፖርት ሜዳ፣ አምስት ዘመናዊ የህዝብ መገልገያ የጋራ መጸዳጃ ቤቶች፣ ደረጃውን የጠበቀ ሰፊ የእግረኞች መንገድ፣ በከተማው ስታንዳርድ መሰረት የተከናወኑ የህንጻዎች እድሳት፣ ፋውንቴኖች፣ የመዝናኛ ፓርኮች እንዲሁም የህዝብ መናፈሻ ቦታዎች የተካተቱበት ነው።

ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የጀመርናቸውን ስራዎች በመደገፍ ይህን ስራ ያሳካችሁ የቦሌ ክፍለከተማ አመራሮችን፣ ድጋፍ ያደረጋችሁ ባለሀብቶችን እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎችን በሙሉ በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከልና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የምናከናውናቸውን ስራዎችን ከነዋሪዎቻችንን ጋር በመተባበር መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.