የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት አቃቂ ክፍለ ከተማ ገላን ጉራ ለሚኖሩ የካዛንቺስ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ማዕድ አጋራ

የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ መኮነን ያዒ በማዕድ ማጋራቱ ወቅት እንደተናገሩይ ነዋሪዎቻችን አዲስ የገቡባቸው አካባቢዎች ለኑሮ የሚስማማ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች እየተሟላላቸው መሆኑን ገልጸው ሰውን ያማከለ ልማትን በማጠናከር በተለይም አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞችን መደገፉ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። ወጣቶች ስራ ሳያማርጡ በተገኘው ዕድል ሁሉ እንዲሰሩም አቶ መኮንን አሳስበዋል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲሱ ሻንቆ(ዕጩ ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የቂርቆስ ነዋሪ የነበራችሁ ነዋሪዎቻችንን በዛሬው ዕለት አይዟችሁ ከጎናችሁ ነን ለማለት ህብረተሰባችንን በማስተባበር ማዕድ አጋርተናል ብለዋል።

መንግስታችንና ፓርቲያችን በሰው ተኮር ተግባር እና በልማቱ በትኩረት በመስራት አዲስ አበባን የአፍሪካ ፈርጥ ለማድረግ እየተጋ መሆኑን የገለጹት አቶ አዲሱ ቀጣይም ህብረተሰቡን በማስተባበር ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በበኩላቸው ከቂርቆስ ካዛንቺስ በልማት ተነሺ የሆኑትን ተቀብለን የተለያዩ መሠረተ ልማት እንዲሟላ በማድረግ የብልፅግናን ሰው ተኮር በተግባር አሳይተናል ብለዋል።

በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እየሰራን ነው ያሉት አቶ አለማየሁ ቂርቆሶች ስላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዛሬው ዕለት ለነዋሪዎቹ የተደረገው ድጋፍ ዱቄት ፣ዘይት፣ ፓስታ፣የተለያዩ አልሚ ምግቦችን ያካተተ መሆኑ ተገልፀዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.