የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ካቢኔ በ3ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ስብሰባው ሶስት ትልልቅ የከተማዋ ደንቦች ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።
በዚሁ መሠረት ካቢኔው ተወያይቶ ያፀደቃቸው ደንቦችም የሚከተሉት ናቸው፦
1ኛ ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አስተዋፅኦን ፣ አገልግሎት እና ማህበራዊ ኃላፊነት አሰራር ለመደንገግ ተዘጋጅቶ የቀረበው ረቂቅ ደንብ፤
2ኛ ፦ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚመሩበትን ሥርዓት እንደገና ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ
3ኛ. የዓድዋ ድል መታሰቢያን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ መርምሮ ከተወያየ በኋላ ለተሻለ የአሰራር ሥርዓት እንዲያመቹ ለማድረግ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.