የአዲስ አበባ ምክር ቤት የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት አነሣ
የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው የአንድ አባሉን ያለመከሰስ መብት አንሥቷል።
የምክር ቤቱ አባል ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን የተነሣው በፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት መሆኑን በምክር ቤቱ የሰላም፣ የፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ አስታውቋል።
ቋሚ ኮሚቴው በሚኒስቴሩ የቀረበውን የሙስና ክስ በመመርመር የደረሰበትን ውጤት ለምክር ቤቱ ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል።
ምክር ቤቱ የቀረበው ሪፖርትን በመመልክት አባሉ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.