ዛሬ የምክር ቤታችንን 4ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ አከናውነን ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱልን ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እንዲሁም ማብራሪያ ሰጥተናል።
ከተማችንን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እና የኑሮ ጫናን ለማቅለል እንዲሁም ዓለምአቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ ያከናወንናቸው ስራዎች ነዋሪዉን ተጠቃሚ ያደረጉ፣ ያስደሰቱ እና ሊበረታቱ የሚገባቸው መሆናቸውን የምክር ቤት አባሎቻችን የገለፁልን ሲሆን የኮሪደር ልማት ተነሺዎች አዲስ የገቡባቸው ቤቶች እና አካባቢዎች ንጹህ ተደርገው፣ መሰረተ ልማቶች በፍጥነት እየተሟላላችው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉበት መንገድ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀውልናል።
በሌላ በኩል ህዝቡ እንዲመለስለት ያቀረባቸው ጥያቄዎችንም ያነሱልን ሲሆን በተለይ የዘገዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች በፍጥነትና ጥራት እንዲጠናቀቁ፣ ያልተፈቱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ እንዲሁም የልማት ተነሺዎች ከማህበራዊ ትስስራቸው ሳይበታተኑ ምቹ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤትና አካባቢ ማዘጋጀታችንን አጠናክረን እንድንቀጥል አሳስበውናል።
በተለወጠ አዲስ የስራ ባህል በጥራትና በፍጥነት በላቀ የኃላፊነት ስሜት የመረጠንን እና እምነት የጣለብንን ህዝብ ዝቅ ብለን ማገልገላችንን እንቀጥላለን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.