አዲስ አበባ በ2035 የአፍሪካ የስበት ማእከል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ በ2035 የአፍሪካ የስበት ማእከል ከተማ እንደምትሆን EIU በዘገባዉ አመላከተ።

EI(ኢ.አይ.) በዓለም ዙሪያ ላሉ ንግዶችና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች መረጃ በሚሰጥ ከፍተኛ ምንጭ የሆነው የኢኮኖሚስት ስብስብ ዋና የምርምርና ትንታኔ ዘርፍ ሲሆን “የአፍሪካ ከተሞች 2035” በፈጣን የከተማ መስፋፋትና የኢኮኖሚ እድገት ላይ በሚል ርዕስ ባወጣው ዘገባ አዲስ አበባ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ከተሞች በግንባር ቀደምትነት አስቀምፃል፡፡

ለዚህም እድገት ነዋናነት ዘመናዊ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ የከተሞች መስፋፋት እና በአቅራቢያው ያሉ ትላልቅ ከተሞች መፈጠር ለከተሞች እድገትና ለወጥ መንስዔዎች መሆናቸውን በመጠቆም አዲስ አበባ በአፍሪካ በጣም ፈጣን የከተማ ኢኮኖሚ በማስመዝገብ እዉቅና በማግኘት አንዷ መሆኗንና  እ.ኤ.አ. እስከ 2035 ድረስ ባለሁለት አሃዝ እውነተኛ የሀገር ውስጥ ምርት እድገትን በፈጣን እድገት እንደምታስመዘግብ በትንበያዉ አመላክቷል፡፡

በአፍሪካ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ እንደ ናይሮቢ እና አቡጃ ያሉ ከተሞች ከ6 በመቶ እስከ 8 በመቶ የእድገት ደረጃ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል በማለት የከተሞችን እድገት ተንቢያል።

ዘገባው አያይዞም እንደ ካይሮ፣ ሌጎስ እና ጆሃንስበርግ ያሉ የአፍሪካ ግዙፍ ከተሞች የኢኮኖሚ የበላይነታቸውን አስጠብቀው እንደሚቀጥሉ ይጠበቃል ሲል ዘገባው እንደ አዲስ አበባ ያሉ ከተሞች በከፍተኛ ፍጥነት የዕድገት ደረጃ ሊያገኙ እንደሚችሉ ይተነብያል።

ዘጋቢ ተቋሙ አፍሪካ በተለይም በከተሞች ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት እየጨመረ በመምጣቱ ፈጣን የህዝብ እድገት እያስመዘገበች መሆኗን በመጠቆም በዚህም በ2023 የአፍሪካ የከተማ ህዝብ ቁጥር ከ650 ሚሊዮን ገደማ  የነበረው በ2035 ወደ አንድ ቢሊዮን እንደሚጠጋ ጠቁሟል። ይህም አጠቃላይ አመታዊ የእድገት ምጣኔ (CAGR) 3.5 በመቶ ሲሆን በ2035 ከ50 በመቶ በላይ አፍሪካውያን በከተሞች እና በከተሞች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚገመት ትንበያውን አስቀምጧል።

ሪፖርቱ  በተጨማሪም ፈጣን የከተሞች መስፋፋት  መጨናነቅን፣ መደበኛ ያልሆኑ ሰፈራዎችን መስፋፋት እና ከፍተኛ የስራ አጥነት ችግሮችን ተግዳሮቶችን እንዳያመጣም አስጠንቅቋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.