የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ 'የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና' በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን ዓውደ ርዕይ ከፍተናል::

ብልጽግና ፓርቲ በሀሳብ ልዕልና በማመን ሀሳብ ይዞ፣ በሀሳብ ልእልና ታግሎ፣ በሀሳብ ልዕልና በህዝብ ተመርጦ ከህዝባችን ጋር ዝቅ ብሎ በመስራት ላይ የሚገኝ የህዝብ ፓርቲ መሆኑን በነዚህ አምስት ዓመታት የተሰሩ ስራዎች የሚመሰክሩና የፓርቲዉን ማንነት እና አላማ በግልፅ የሚያሳዩ ናቸው::

አዲስ አበባን እንደስሟ ዉብ አበባ እናደርጋታለን ብለን ከተማችንን ጽዱ፣ ውብና ለኑሮ ተስማሚ፣ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል በማድረግ ቃላችንን በተግባር በመፈጸም እንዲሁም ለሰው ልጆች ቅድሚያ በመስጠት በልማት ስራዎቻችን የነዋሪውን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሰው ተኮር ስራዎችን ሰርተን የበርካቶችን እምባ አብሰናል::

ሆኖም መንገዳችን የሃሳብ ድቀት ባላቸዉ ኋላ ቀሮች ምክንያት ተግዳሮት እና ችግር አልባ አልነበረም። ባጋጠሙን ፈተናዎች ከጐናችን ያጣናቸዉና በመንገድ የቀሩም ነበሩ:: ነገር ግን ፓርቲያችን አሁንም በፅናት እና በድል ወደፊት ቀጥሏል ።

አሁንም ቃላችንን አድሰን፣ ተግዳሮቶችን አስወግደን እና እጅ ለእጅ ተያይዘን በጀመርነው መንገድ ህዝባችንን ዝቅ ብለን የምናገለግልበት እንዲሁም የኢትዮዸያን ዘላቂ ሰላም እና ብልፅግና በማረጋገጥ በላቅ ትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.