የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መርካቶ ሸማ ተራ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ በነበረው የእሳት አደጋ ሱቅ የተቃጠለባቸው ነጋዴዎችን በጊዜያዊነት መልሶ ለማቋቋም የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጏል::

በድጋፍ መርሃ ግብሩ ወቅት ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አካባቢው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ መልሶ እስኪገነባ ሱቅ ለተቃጠለባቸው ነጋዴዎች የመስሪያ ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ከተደረገው የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በተጨማሪ የአይነት እና የቴክኒክ ድጋፎችን እናደርጋለን ብለዋል::

በአካባቢው ያለውን ጥግጊትና መጨናነቅ በዘላቂነት በመቅረፍ፣ የተሽከርካሪ መንገድን በማካተት እንዲሁም ለአደጋ ተጋላጭ በማያደርጋቸው መልኩ በዘላቂነት በአክሲዮን ተደራጅተው ደረጃውን የጠበቀ የገበያ ማዕከል መገንባት እንዲችሉ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ከንቲባ አዳነች ጨምረው ገልጸዋል::

ድጋፉን የተቀበሉት የአካባቢው ነጋዴ ተወካዮች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ አደጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ላደረገው ድጋፍ እና ክትትል አመስግነው ድጋፉ በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያደርጋቸው መሆኑን ተናግረዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.