የ’ጥራት መንደር’ን ዛሬ በይፋ ከመመረቃችን ቀደ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የ’ጥራት መንደር’ን ዛሬ በይፋ ከመመረቃችን ቀደም ብሎ የገነባነውን ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማታችንን ትናንት የመጎብኘት እድል ነበረኝ።

ይኽ ወሳኝ ተቋም የሀገር ውስጥ ምርቶቻችን በአለም ገበያ የሚኖራቸውን ተወዳዳሪነት በማላቅ በአለም የእሴት ሰንሰለት የሚኖራቸውን ተሳትፎ የሚያጎለብት ነው።

ከሀገራችን መሪ ተቋማት አንዱ በመሆን የውጭ ንግድ አቅሞቻችንን በማጠናከር በአለምአቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ሆነን እንድንዘልቅ የሚያስችለንም ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.