የከተማችን ውስን ሃብት የሆነውን መሬትን በዘመናዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ እየተሰራ ያለውን የዲጂታላይዜሽን እና የሪፎርም ስራ ተመልክቻለሁ:: ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በዘርፉ ላይ ያለውን የባለ ጉዳይ እንግልት እና ብልሹ አሰራሮችን የሚያስቀር እንዲሁም ለተገልጋዮች ቀላልና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የዲጂታላይዜሽን ስርዓት አበልፅገን ለአገልግሎት ዝግጁ አድርገናል::
የዲጂታላይዜሽን ስራው ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተሞች ያለውን መሬት በአንድ ማዕከል እንድናስተዳድር አቅም የሚፈጥርልን ሲሆን ሲስትሙ በየደረጃ ያለውን አገልግሎት ክትትል ለማድረግ እና ለተገልጋዮች ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለን ይሆናል::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.