የዘንድሮውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የዘንድሮውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በተሻለ ሁኔታ ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንገኛለን።

በዚሁ መሰረት ዛሬ ከሆቴል ባለቤቶች እና ከዘርፉ አካላት ጋር ተወያይተናል።

በውይይቱ እንደተለመደዉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትንና እንግዳ ተቀባይነታችንን አጉልተን በማሳየት በላቀ አገልግሎት ሰጪነት እንድናስተናግድ እንዲሁም ከተማችንን የቱሪዝምና የኮንፍራንስ ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ስራ ይበልጥ በሚያጠናክር አግባብ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ትላልቅ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉባኤዎች ወደ ከተማችን እንዲመጡ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ተግባብተናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.