አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈታ የህዝብ ድምፅ የሆነ ሚዲያ ነው ፦ወ/ሮ እናታለም መለሰ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ እና
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ
የአዲስ አበባ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ እና
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ እናታለም መለሰ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈታ የህዝብ ድምፅ የሆነ ሚዲያ ነው ብለዋል።
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በከተማዋ የሚከናወኑ የልማትና የፈጠራ ስራዎችን እንዲሁም ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸውን መረጃዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ በዜናና በዶክመንተሪ ና በፕሮግራም ለህብረተሰቡ ተደራሽ በመሆን የትውልድ ድምፅ መሆኑን አረጋግጧል።
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ በስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽንና አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ዓላማቸውም ግባቸውም አንድ ነው ብለዋል።
ሚዲያው ህዝብና መንግስትን በማገናኘት በቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆን ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል። የሚዲያው ሎጎ የሆነው የዋርካ ፕሮግራም የመጣውን ለውጥ አጠናክሮ በማስቀጠል በሌሎችም አዳዲስ ስራዎች ለተመልካቾች በቅርቡ ወደ ተመልካቾች እንደሚደርስ ተናግረዋል። ሚዲያው ከተቋማት ጋር የሚያደርገውን ቅንጅታዊ ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ዋርካ ፕሮግራም የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ህብረተሰቡንና መንግስትን በማስተሳሰር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ትልቁን ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ፕሮግራም እንደሆነ ተጠቅሷል።
የሁለቱ ተቋማት የመግባቢያ ስምምነት በተለየዩ የሙያ በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የሚታዩትን ተግዳሮቶች የሚቀርፍና የአዲስ ሚዲያን ተደራሽነቱን ከፍ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።
በስምምነት መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አመራሮች ተገኝተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.