በከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኝነት በመዲናችን አዲስ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በከተማ አስተዳደሩ ቁርጠኝነት በመዲናችን አዲስ አበባ የተሽከርካሪ ምርመራን በእጅጉ የሚያዘምን አዲስ ማሽን ትግበራ እንደሚጀምር ተገለጠ "በዘርፉ_የሚታየዉ ማጭበርበር_ማክተሙ እዉን_ይሆናል!"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደድር የተቋማት ሪፎርምን ውጤታማ በማድረግ፣ የከተማችንን ነዋሪ ጥያቄዎች ለመፍታት ሰፊ ርብርብ በማድረግ ላይ መሆኑና በዚህም ዘመናትን ያስቆጠሩ በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመፍታት ውጤቶች መገኘታቸዉን ገልጧል፡፡

በፕሮጀክት አፈፃፀም እጅግ አመርቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ ቢሆንም ለከተማችን ነዋሪዎች በሚገባው ልክ አገልግሎት ማቅረብ እና ዕርካታን ከማረጋገጥ አንፃር ረጅም ርቀት የሚቀረን መሆኑን በማመን የከተማው ኮር አመራር ቁርጠኛ አቋም በመውሰድ ተገልጋይ የሚበዛባቸውን 16 ተቋማት ሪፎርም በማድረግ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አበረታች ውጤት እየተገኘ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አመላክቷል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በፊት ሰፊ የህዝብ ሮሮ እና እንግልት ከሚበዛባቸው ተቋማት ውስጥ አንዱ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን መሆኑን ጠቅሶ ከሪፎርሙ በኋላ የተሻለ አገልግሎት በተቋሙ ለማስፈንና የተገልጋይ ዕርካታን ለማሻሻል እና አመኔታን ለማረጋገጥ ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ ብሏል፡፡

በተወሰደዉ ቁርጠኛ አቋም ለሌብነት እና ለብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሆነው የተሽከርካሪ ምርመራን የሚያዘምን HD Industrial Endoscope ማሽን መሆኑን ጠቅሶ ማሽኑ የተሽከርካሪ ሻንሺ ቁጥር፣ የሞተር ቁጥር እና የትኛውንም የተሽከርካሪ አካል ትክክለኛነት ማረጋገጥ የሚያስችል እጅግ ዘመናዊ መሳሪያ ነዉም ብሏል።

የከተማ አስተዳደሩ በተቋሙ የተሽከርካሪ ምርመራ ማሽንን በቅርቡ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጀምርና ከዚህ ማሽን ትግበራ በኋላ በተመሳሳይ ሻንሺ ቁጥር እና የሞተር ቁጥር በዘርፉ የሚታየዉ መጭበርበር ማክተሙ እዉን ይሆናል ተብሏል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.