የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽሮች በቻ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽሮች በቻይና ቤይጂንግ የሀገራት ዋና ከተሞች የህዝብ ደህንነት 2024 ጉባኤ ላይ በመገኘት በአዲስ አበባ ከተማ የሚከናወኑ የፀጥታና ደህንነት ሥራዎች ምርጥ ተሞክሮዎችን ማቅረባቸው ተገለፀ።

ከአፍሪካና ከመላው ዓለም የተውጣጡ የአስራ ስምንት ሐገራት የፖሊስና የፀጥታ አካላት የተሳተፉበት የሀገራት የዋና ከተሞች የህዝብ ደህንነት 2024 ጉባዔ (Metropolitan Public Security conference 2024) በቻይናዋ ዋና ከተማ ቤይጂንግ ተካሂዷል፡፡

እ.ኤ.አ. ከDEC 25-27 በተካሄው ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውና የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ በጉባዔው ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በህዝባዊ ቻይና ሪፐብሊክ ምክትል የህዝብ ደህንነት የተከበሩ ሺ ያንጁን ኢትዮጵያን ወክለው በጉባዔው ላይ ለተሳተፉት የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽነሮች የክብር አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በጉባዔው ላይ የአዲስ አበባን የፀጥታና ደህንነት አጠባበቅ ( Best practices of Addis Ababa) በሚል ርዕሰ - ጉዳይ ላይ ያተኮረ ተሞክሮ ለሀገራቱ ዋና ከተማ ተወካዮች በገለፃ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው አዲስ አበባ ፖሊስ የከተማዉን ፀጥታና ደህንነት ለማረጋገጥ በተለይም የአደንዛዥ ዕጽ ዝውወር߹ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርንና ሌሎች ወንጀሎችን ከመቆጣጠር አንፃርና የከተማችንን ፀጥታ ለማስጠበቅ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራትና የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በተመለከተ ተሞክሮ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በህዝባዊ ቻይና ሪፐብሊክ ከምክትል የህዝብ ደህንነት ሺ ያንጁን ጋር አዲስ አበባ ፖሊስ ከቤጂንግ ፖሊስ ጋር ቀጣይ በሚኖረው የትብብር ግንኙነት ዙሪያ የጎንዮሽ ውይይቶች አድርገዋል። የዜጎችን ሠላምና ደህንነት በማስጠበቅ ዙሪያ በፀጥታ ኃይሉ የሚከናወኑ ተግባራት የሀገራችንን የተቀባይነት ደረጃ ያሳየና የአዲስ አበባ ፖሊስ የተልዕኮው ስኬት ማሳያ ነው።

በጉባዔው ፖሊስ በሪፎርም ስራዎቹ ያከናወናቸውን የቴክኖሎጂ እመርታዎች፣ ህገ-ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አድርጎ የመጠቀም ወንጀልን ለመቀነስ የተሰሩ የቅድመ ወንጀል መከላከል ሥራዎችን፣ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ምርጥ ተሞክሮዎችና በተለይም እንደ ፀጥታ ተቋም የሽብርተኝነት ወንጀልን ለመከላከል እየተከናወኑ የሚገኙ ውጤታማ ተግባራትን ለጉባዔው ተሳታፊዎች ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በገለጻቸው አቅርበዋል፡፡

ጉባዔው አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ሁሉን አቀፍ ተቀባይነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ምቹ መደላድልን የፈጠረ ከመሆኑም ባሻገር የአዲስ አበባ ሠላማዊነት ከተማዋ ለቱሪዝም መዳረሻነት ያላት ተመራጭነት ያስተዋወቀ ጉባዔ እንደነበረ ተገልጿል፡፡

ባለፈው ወር በተከበሩ ሺ ያንጁን የህዝባዊ ቻይና ሪፐበሊክ ምክትል የህዝብ ደህንነት የተመራ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ፖሊስ የስራ ጉብኝት ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.