የከተማዋን የገበያ ስርዓት ከማረጋጋት አኳያ ህ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የከተማዋን የገበያ ስርዓት ከማረጋጋት አኳያ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በጋራ ልንከላከል ይገባል፦ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመርካቶ የሚስተዋለውን ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በመከላከል ረገድ የተሰሩ ስራዎችን በመገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

በመድረኩም አዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሻለቃ ዘሪሁን ፣ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድርና የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል እንዲሁም ሌሎች የከተማና የክፍለ ከተማው አመራሮች እና የፀጥታ ሃይሎች ተሳትፈዋል።

በግምገው ወቅትም የንግድ ክትትልና ቁጥጥሩን ከወትሮ በተለየ መልኩ በቅንጅታዊ አሠራርና ፈረቃ በማጠፍ ጭምር 7/24 በመሥራት ገበያው እንዲረጋጋና የህግ የበላይነት እንዲሰፍን ከፍተኛ ስራዎች እየተሰራ መሆኑንም ገልጿል።

በዚህም ያለ ንግድ ፈቃድ በሚሠሩ፣ ፈቃድ ሳያሳድሱ በሚሰሩ፣ ምርት ወይም ሸቀጥ በሚደብቁና በግብይት ወቅት ደረሰኝ በማይቆርጡ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ተገምግሟል።

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በዉይይቱ ላይ እንደተናገሩት በአካባቢዉ ላይ ህጋዊ የግብይት ስርዓት እንዲሰፍን ከሚመለከታቸው የግብረ-ሃይሉ አባል ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረው በቀጣይም የከተማዋን የገበያ ስርዓት ከማረጋጋት አኳያ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በጋራ ልንከላከል ይገባል ብለዋል።

አሁን እየተሰራ ያለዉ የህግ የበላይነት የማስፈን ስራ እንዲጠናከር በማድረግ ምርት እያለ የለም በሚሉ አስመጪዎችና ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተናግረው ያለ ደረሰኝና ያለ ንግድ ፈቃድ በሚያከፋፍሉ አስመጪዎች፣ አምራቾችና ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥሩ በማጠናከር ወደ ህጋዊ ስርአት እንዲገቡ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ወ/ሮ ሊዲያ አክለውም ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በቅንጅት ህገ-ወጥነትን ለመከላከልም ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ገልፀው በከተማዋ በሚካሄደው የግብይት ስርአት ላይ በሁሉም ክ/ከተሞች የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በተጀመረዉ አኳኋን መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.