መረጃ እንደየ ሰው በጎ ፈቃድ በሚተነተንበት አ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

መረጃ እንደየ ሰው በጎ ፈቃድ በሚተነተንበት አሁን በምንገኝበት የድህረ እውነት ዘመን ሚዛናዊነታችንን ጠብቀን መረጃዎችን ከምንጫቸው በመውሰድና ትክክለኝነታቸውን በማረጋገጥ ለሕዝብ ተደራሽ ልናደርግ ይገባል ::"የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትአለም መለሰ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየደረጃው የሚገኙ የኮሙኒኬሽን መዋቅር የቀጣይ የመረጃ እና የኮሙኒኬሽን እስትራቴጂ ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ የኮሙኒኬሽን የቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ እናትአለም መለሰ እንደተናገሩት መረጃ እንደየሰው በጎ ፈቃድ በሚተነተንበት አሁን በምንገኝበት የድህረ-እውነት ዘመን ተቋማዊ ሚዛናዊነትን ጠብቀን መረጃዎችን ከምንጫቸው በመውሰድና ትክክለኛነታቸውን በማረጋገጥም ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ የሕዝቡን የመንግሥት መረጃ ፍላጎት ማርካት ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል ።

ጥንካሬያችንን በማጉላት ሀገራዊ ሪፎርሙን ተዋህደን በጋራ ልንመራ ይገባልም አክለው ያሉት ቢሮ ኃላፊዋ ሌሎችንም ተቋማት ተቀናጅተን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ የመደገፍ ነባር ልማዳችንን አጠናክረን ልናስቀጥል ይገባልም ብለዋል ።

ቢሮ ሃላፊዋ አክለውም በቀጣይ በትኩረት አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን የመጀመሪያው የመንግስትን የፖሊሲ ማዕቀፍ መነሻ አድርገን የኮሪደር ልማት ፣ የሜጋ ፕሮጀክቶች የግንባታ እንቅስቃሴ ፤ብልሹ አሰራርን መታገል ፤ህግና ስርዓትን ማረጋገጥ ፤የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው መሬት እንዲነካ ለማስቻል የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር ፤መልካም አስተዳደርን ማስፈን ፤ገበያ ማረጋጋት ፤ጤናማ የንግድ እንቅስቃሴ መጎልበት ፣ገቢን በሚፈለገው አግባብ መሰብሰብ መቻል ፤ሥራ ዕድል ፈጠራ፤የፋብሪካና የግብርና ምርት ሕጋዊ የገበያ ሰንሰለት ጠብቆ ለሕዝብ እንዲደርስ ማስቻል የሚሉት የቀጣይ ጊዜያት የትኩረት ስራዎች ናቸው ብለዋል።

በመጨረሻ በመድረኩ የተናገሩት የኮሙኒኬሽን መዋቅር አመራር እና ዳይሬክቶረች የተቋም ሁለንተናዊ ግንባታና ልዕልናን ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራርን መከተል ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.